ታሪክን የኋሊት መጅሊስ መቸ ተመሰረተ ትግሉስ መቸ ተጀመረ እነ ሸህ ሰዒድስ የተሰደዱበት የ1987ቱ አውሃል ምን ይመስል ነበር?

ታሪክን የኋሊት መጅሊስ

“በአቡበክር የሚመራው የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ እንደት ተቋቋመ፣ የኮሚቴውስ አላማ ምን ነበር” ቀንጨብጨብ ተደርጎም ቢሆን ተዳሷል።

ከዘመናት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በተለይ ከኡለማዎች (የሐይማኖት አባቶች)እልህ አስጨራሽ ትግል በሁዋላ መጅሊስ መጋቢት 4 ቀን 1968 “የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባዔ” በሚል ስያሜ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ሃይማኖታዊ ጉዳዮች የበላይ ተጠሪ አካል እንዲሆን ተብሎ ተመሰረተ። መተዳደሪያ ደንቡም ይህንኑ ስልጣን በሚያጸና አኳኋን ተረቀቀ፡፡

በወቅቱም 50 አዲስ አበባ የሚኖሩ ዑለሞችና (የሃይማኖት አባቶች) ኢማሞች ከየብሔረሰቡ ተውጣጥተው በመሪነት ቦታው ላይ እንደተቀመጡ ይነገራል፡፡ የዛኔው መጅሊስ የብሄር ተዋጽኦ ብቻ ሳይሆን የሙያ እና የእድሜ ስብጥርን ታሳቢ በማድረግ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችንም በውስጡ በማሳተፍ 4 ዓይነት የአባልነት ወንበሮችን አስቀምጦ ነበር።

በዚህም ግማሽ አባላት ዑለማዎች መሆን ያለባቸው ሲሆን፣ 30 በመቶ ምሁራን፣ 10 በመቶ አዛውንቶች፣ እንዲሁም 10 በመቶ ወጣቶች በተቋሙ ውስጥ ውክልና እንዲኖራቸው ታሳቢ ተደርጓል፡፡ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ሊቀመንበርነትና በሐጂ ኢብራሒም ዐብዱሰላም በተጨማሪ እንዴነ የኑስ ፈቂህ፣ ሐጅ ኡመር ኢማም፣ሀጅ ማህሙድ ሙዳወር፣ሐጅ ሙሃመድ ሲራጅ፣ሐጅ ሻሚል ኑርሰቦ፣ሐጅ ሙሀመድ ኢድሪስ፣ሐጅ ሸረፋ ሙሃመድ እና ሀጅ ሙሃመድ ቱሬ የመሳሰሉ ኡለማዎች መጅሊስን በመመስረት አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

እነዚህ ተላላቅ አሊሞች እንደስካሁኖቹ መጅሊስ አመራር ተብየዎች የመንግስት ሴራ አስፈጻሚ ሳይሆኑ ይልቁንም ከደርግ መንግስት ከፍተኛ ጫና እንደሚደርስባቸው ይነገራል፡፡ ለምሳሌ ሐጅ ሙሃመድ ሳኒ ልጅን መንግስት እንደረሸነባቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በወቅቱ የነበሩ የመጅሊስ አመራሮች ደሞዝ ያልነበራቸውና በበጎፈቃድ ለአላህ ብለው ብቻ እንደሚያገለግሉ ይነገራል፡፡ እስከዛሬ የነበሩትን ታውቋቸዋላችሁ። መጅሊስ ሲቋቋም የሚከተሉትን ዋና ዋና አለማዎችን አንግቦ ነበር፡፡ እነሱም

1. ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በመንፈስ ረገድ ማደራጀት፣
2. ሃይማኖታዊ ትምህርትን ማስፋፋት፣
3. የሃይማኖታዊ ትምህርት ተቋማትን ማደራጀት፣
4. መንፈሳዊ ጽሑፎች በአገርኛና ሌሎች አገረኛ ቋንቋዎች እንዲተረጎሙ ማድረግ፣
5. ወቅፎችን(በሱጦታ የተበረከቱትን) በበላይነት መቆጣጠር፣
6. አዳዲስ ንብረቶች የሚገኙበትን መንገድ መቀየስና መተግበር፣
7. በልማትና በአገር ግንባታ ረገድ መሳተፍና መተባበር ናቸው። መጅሊስ ከተመሰረተ 1968 እስከ 1985 ድረስ ምንም እንኳ በመንግስት ጫና ምክናየት ያቀደውንና የሚጠበቅበትን ያክል ሰርቷል ማለት ባያስደፍርም አቅሙን አሟጦ ያለምንም የውስጥ ልዩነት ለህዝበ ሙስሊሙ የቆመና ህዝበ-ሙስሊሙም ሙሉ እምነቱን የሚጥልበት ተቋም ነበር፡፡

ነገር ግን ኢህአደግ ስልጣን ከያዘ ከጥቂት አመታት በህዋላ ማለትም ከ1985 ጀምሮ በመጅሊስ ውሥጥ ክፍፍል ማስተዋል ጀመረ፡፡ በዚህም የመጅሊስ ክፍፍል የመንግስት እጅ እንዳለበት ይታመናል፡፡ የ1987ቱ ታሪካዊ ደም አፋሳሽ ግጭትም በሙስሊሞች መካከል ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ክስትት ብቻ ሳይሆን የእስከዛሬው የህዝበ-ሙስሊሙ ንትርክ ዘር ዘርቶ ያለፈ ክስተትም ነበር፡፡

ከዚህም ግጭት ጋር ተያይዞ እነ ሐጅ ሙሐመድ ወሌን ጨመሮ ሌሎች ታላላቅ አሊሞች ወደ ከርቸሌ ወርደው ነበር፡፡ ብዙዎቹ እስከ3 አመት ከታሰሩ በህዋላ ተፈታዋል፡፡መንግስት እጁን አስገብቶበታል የሚባለው የ1985 የመጀመሪያው አገር አቀፍ ምርጫ በተካሄዴ በማግስቱ መጅሊስ ከላይ ከተዘረዘሩት አላማዎች በተቃራኒው በመሄድ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ድርጅት ወይም ኢ.ሙ.ወ.ድ (በአጭር የአረብኛ አጠራሩ ሙነዘማ) እየተባለ የሚጠራውን በሽግግር መንግስቱ እውቅና ያገኘውን የህዝበ-ሙስሊሙን ማህበርና ሌሎች ኢስላማዊ ማህበራቶችን ከመንግስት ጋር በመሆን ከምድረ-ገፅ እንድጠፉ አስደረገ፡፡ እንግድህ ይህ የሚያሳየን መጅሊስ የእስከዛሬውን ተግባር “ሀ” ብሎ መለማመድ የጀመረው በ1985 ነበር ማለት ነው፡፡

የ1987ቱን ግጭት ተከትሎ በ1988 የተመረጡት የመጅሊስ አመራሮች የተወሰነ ጥሩ ስራ ቢሰሩም ተቋሙን (መጅሊስን) ከጀመረው የቁልቁለት መንገድ ግን መታደግ አልቻሉም፡፡ ይልቁንም በ1992 ምርጫ መልሰው እራሳቸው እንዲመረጡ በማድረግ የቁልቁለት መንገዱን የበለጠ እንድፋጠን አደረጉ፡፡በ1996 እና በ1997 ለማካሄድ የታሰበው የመጅሊስ ምርጫ ሳይካሄድ ቀረ፡፡ ከዚያ በህዋላ እስከ ዛሬ 1 ወር በፊት የመጅሊስ አመራሮች ማን እንደመረጣቸውና እንዴት እንደተመረጡ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡

በመሆኑም የመንግስትን አላማ በህዝበ-ሙስሊሙ ላይ ለመጫን የተስማሙ ቡድኖች መጅሊስን ተቆጣጥረው ህዝበ ሙስሊሙን በተለያየ (በድናዊና ቁሳዊ) መንገድ መበዝበር ጀመሩ፡፡ ከዚያም ባንድ መንገድ መጅሊሱ ጥሩ ግንዛቤ ያላቸው ወጣቶችን ያመርታል ብሎ ያሰበውን ብቻውን የሙስሊሙን ተቋም አወሊያ ት/ትና ኮሌጅን በ2004 ለማዘጋት እቅድ አውጥቶ ወደ 50 የሚሆኑ የአረበኛ መምህራኖችን በማባረሩ በተፈጠረ ችግር, ሁለትም መንግስት ሀጋይ እርሊች (Haggai Erlich) የሚባለውንና በከረረ የጸረ-ሙስሊም አቋሙ የሚታወቀውን አይሁዳዊ የታሪክ ፕሮፌሰር ስለ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥናት ካሰሩ በህዋላ ፕሮፈሴሩም አህባሽ የሚባለውን እምነት አምጥቶ በመጫን በመነቃቃት ላይ ያለውን ህዝበ-ሙስሊም ማዳከም ይቻላል ብሎ ጥናቱን ባቀረበው መሰረትና መንግስት ከመጅሊስ ጋር በመተባበር አህባሽ የተባለ ሴክትን በግዳጅ ህዝበ-ሙስሊሙ ላይ ለማስረጽ በመሞከሩ ህዝበ ሙስሊሙ የደለበ ብሶቱን ጨምሮ የ ስሙኝ ጥሪውን ማሰማት ጀመረ፡፡

ከዚያም ህዝበ ሙስሊሙ ጁማዓ ጁማዓ ለሰላት ሲገናኝ በሀገሪቱ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ ሰላማዊ ግን እጅግ አስፈሪ ተቃውሞ ማሰማቱን ተያያዘው፡፡ የዚህን ህዝብ ብሶት የሚያሰማ እስር ላይ የቆዩትን ግዚያዊ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴም ተቋቋመ፡፡መጀመሪያ መፍትሔ ለማፈላለግ በህዝበ ሙስሊሙ በቀጥታ የተመረጡት የኮሚቴው አባላት ወዴ 29 የሚደርሱ ቢሆንም በህዋላ መጨረሻ ላይ በአቡበክር አህመድ ሰብሳቢነት የሚመራው 17 አባላት ያሉት ኮሚቴ ቋሚ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሆኖ ቀጠለ፡፡ እዚህ ጋር ልብ ትሉት የሚገባው የዚህ ኮሚቴ አላማ መፍትሄ ማፈላለግ ሲሆን መፍትሄ ከተገኘ በህዋላ የሚፈርስ (ad hoc) ኮሚቴ ነው፡፡ ይህንን ኮሚቴ መጀመሪያ መንግስት በይፋ እውቅና ሰጥቶ በሰላም ቢያነጋግርም በህዋላ ግን በመጅሊስ ጉትጎታ መንግስት ነገሩን ወዴ አልሆነ ነገር ሆን ብሎ ስለጠመዘዘው የኮሚቴዎቹ አባላት የከፈሉትን መስዋዕትነት ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያውቀው ነው፡፡ በዚህ ውጣ ውረድ ውስጥ ከ2004-2010 ባለው ግዜ በኮሚቴውና በአጠቃላይ በህዝበ-ሙስሊሙ ላይ መንግስት ከመጅሊስና መሰል አጋሮች ጋር ሁኖ ያደረሰው ግፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ምእራፍ ተሰጥቶት በአሳዛኝነቱም ሆነ በአስተማሪነቱ እንደሚከተብ አልጠራጠርም፡፡ ከዚህ ሁላ መከራ ቡሃላ ነው። በ23 ዓመታቸው እነ ሸህ ሰዒድ ዛሬ ወደ ሃገራቸው የገቡት።

Latest News

video image video image video image Read More

Get Connected

logo link youtube logo link twitter logo link facebook

Contact Information