Ethiopia: ሙስሊሙ ዘር የለውም ሙስሊሙ እኔ አማራ ነኝ እኔ ኦሮሞ ነኝ እኔ ትግሬ ነኝ አይለም ለምትሉ አንብቡ።

beautiful girls
ቅን ዘረኝነት||
ዘረኝነት ማለት ለዘር መቆርቆር ከሆነ
ዘረኝነት በመልካም ስራ በልጦ ለመገኘት ከሆነ
ዘረኝነት በሰናይ ተግባር እና በፈሪሃ አሏህ ለመተጋገዝ ከሆነ
ዘረኝነት ድህነትን እና ችግር በጋራ ለመዋጋት ከሆነ
ዘረኝነት ዲናችን በኛ በኩል መጠቃት የለበትም በሚል መንፈስ ከሆነ
ዘረኝነት ሀገር ለማልማት ከሆነ
ዘርኝነት ወገንን ለመርዳት ከሆነ
ዘረኝነት የራስን ብሄርህ የማላቅና ሌላውን የመናቅ ኩራት የሌለበት ከሆነ
ዘረኝነት የሌላውን ብሄር ፀጋ በመመቀኘት ካልሆነ … ወዘተ
ዘረኝነት ከላይ በተዘረዘረው መሰረት ከሆነ መልካምና የሚበረታታ ነው።
የነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ባልደረቦች በተናጥል፣ በቡድንና በጎሳ ለመልካም ስራዎች ይፎካከሩ ነበር። አቡ በከር እና ዑመር ፣ሙሃጂሮች እና አንሷሮች፣ አውስ እና ኸዝረጆች እና ሌሎችም አንዱ ከሌላው በልጦ ለመገኘት ይወዳደሩ ነበር። ነቢዩም (ሰ ዐ ወ) በተለያየ አጋጣሚ ይህን የውድድር መንፈስ በውስጣቸው ያቀጣጥሉ ነበር!
የሲራው ሊቅ ሙሐመድ ብኑ ኢስሓቅ ከዐብዱላሂ ብኑ ከዕብ ብኒ ማሊክ ቀጣዩን ንግግር አስተላልፈዋል: “አሏህ ለነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ከዋለላቸው ውላታዎች ውስጥ… አውስ እና ኸዝረጅ ልክ እንደ ሁለት የግመል ኮርማዎች ይፎካከሩ ነበር፤ አውሶች አንድ (መልካም) ነገር ከሰሩ ኸዝረጆች በዚህ ተግባር ሊበልጡን አይገባም ይላሉ… አውሶችም እንዲሁ! አውሶች ከዕብ ብኑል አሽረፍ የሚባለውን (አማፂ) በገደሉ ጊዜ ኸዝረጆች እንደ ከዕብ ብኑ አሽረፍ ረሱልን ያስቸገረ ሰው ማን አለ?! ሲሉ ተወያዩ ከዚያም መኖሪያውን ኸይበር ያደረገውን ሰልላም ብኑ አቢል ሑቀይቅ (አቢ ራፊዕ) የሚባለውን አማፂ ጠቀሱ…”
[ፈትሑል ባሪ: 7/342]
ረሳልችን (ሰ ዐ ወ) ሲዘምቱ አብረዋቸው ለሚዘምቱ ዘማቾች በጥቅሉ ሙሃጂር እና አንሷር በሚል ከፍለው ሁለት ታላላቅ ባንዲራ ለተወካዮቻቸው ያስይዙ የነበረ ሲሆን… ወረድ ብለው ደግሞ እያንዳንዱ ጎሳ በመሪያቸው አማካይነት ጥቃቅን ባንዲራዎች እንዲይዙ ያደርጉ ነበር።
አል ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ይላሉ:
“ነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ሲዘምቱ እያንዳንዱ ጎሳ በስሩ ሆነው የሚዋጉበትን ባንዲራ ለመሪያቸው ይሰጡ ነበር።”
[ፈትሑል ባሪ: 6/127]
በበኩላቸው ኢብኑ ዐሳኪር እንዲህ ብለዋል:
“የተቡክ ዘመቻ እለት እያንዳንዱ የአንሷር ጎሳ የግል ባንዲራ እንዲኖራቸው አዘዙ፤ የተለያዩ የዐረብ ጎሳዎችም እንዲሁ ባንዲራዎች እንዲኖራቸው አዘዙ።”
[ታሪኹ ዲመሽቅ: 2/36]
ነቢዩ (ሰ ዐ ወ) ይህን ያደርጉ የነበረው ሁሉም ጎሳ በፉክክር መንፈስ በባንዲራቸው ስር ሆነው ታላቅ ጀብድ እንዲሰሩ እንዲሁም በነሱ በኩል ክፍተት ተፈጥሮ ዘማቹ ለክስረት እንዳይዳረግ የቻሉትን ያህል እንዲታገሉ በሚል ሀሳብ ነው ይላሉ ዑለማዎች። በሌላ ቋንቋ ዲናችን በጎሳችን ጀግንነት አማካይነት የበላይ ማድረግ አለብን እንዲሁም በኛ በኩል መጠቃት የለበትም የሚል የፉክክር መንፈስ እንዲፈጠርባቸው ማለት ነው።
ዘረኝነት እንዲህ ሲሆን ጥሩ ነው።
የአማራ ተወላጅ የህዝብ መገልገያ ሆስፒታል ሲሰራ
ኦሮሞው ደግሞ እኛስ ከማን አንሰን ብለው ትምህርት ቤት ቢገነቡ
ትግሬው ደግሞ እኛም ለህዝብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ በማቅረቅ ቢወዳደሩ…
የጉራጌው ተወላጅ ደግሞ በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ ቢፎካከር
ሱማሌው፣ አፋሩ፣ ስልጤው፣ ሀረሪው፣ ሲዳማው ወዘተ በዚህ መልኩ ለእምነት፣ ለሀገርና ለህዝብ በሚጠቅም ነገር ቢወዳደሩ ምን የሚያምር ዘረኝነት ነው?!
ነገር ግን አጥንቴ ካጥንትህ፣ ስጋዬ ከስጋህ፣ ቀለሜ ከቀለምህ ይበልጣል እያሉ ለጥፋት፣ ለጦርነት፣ ለሌብነትና ለዝርፊያ በጥቅሉ በወንጀልና በበደል ለመተባበር ዘርና ብሄር መቁጠር ጥንብ አንሳነት ነው። ምክንያቱም ዘረኝነት በዚህ ትርጉም ጥንብና ድንቁርና ነውና።
የሰው ልጅ የማንኛውም ጎሳ ውጤት ይሁን በተፈጥሮው አንድ ነው። መነሻው አፈር ነው። አባቱ አደም ነው። ማንም ከማንም አይበልጥም አማራው ከሶማሌው፣ ኦሮሞው ከስልጤው፣ አፋሩ ከጉራጌው… አይበልጥም አሏህን በመፍራትና መልካም ስራ በማብዛት ቢሆን እንጂ!
በልጦ ለመገኘት የፈለገ ብሄር ዘረኝነትን በመልካም ትርጉሙ ሊረዳው ግድ ይላል።

Latest News

video image video image video image Read More

Get Connected

logo link youtube logo link twitter logo link facebook

Contact Information