Ethiopia: ኤል ቲቪ ውድ የኤልቲቪ ተመልካቾችቻችን ኤልቲቪ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የሚዲያውን ምህዳር የተቀላቀለ..


እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ይዟቸው በመጣው የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና የዜና ዘገባዎች በርካታ ተመልካቾችን ማፍራት የቻለ ተቋም ነው፡፡

እንደሚታወቀው እያንዳንዱ የሚዲያ ተቋም በኢዲቶሪያል መመሪያው መሰረት የተለያዩ የትኩረት አቅጣጫዎችን በመንደፍ ወደ ህዝብ እንደሚቀርብ ይታወቃል፡፤ኤልቲቪ ኢትዮጵያም በአብዛኛው አስተማሪና አሳዋቂ በሆኑ በማህበረሰብ ለውጥና በመልካም ዜጋ ግንባታ ላይ ያተኮሩ መረጃዎችን የማድረስ ዓላማን አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

በቀርብ ጊዜ በተደረገው አዲስ የመንግስት መዋቅር የሀገራችን የሚዲያ ነጻነት በእጅጉ መሻሻሎችን እያሳየ በመምጣቱ የሚዲያ ተቋማት በነጻነት የህዝብ ድምጽ በመሆን እያገለገሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡

እኛም በሳልና አከራካሪ የሆኑ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያ ጉዳዮችን በጥልቀት በመዳሰስ ለዘመናት በፍርሀትና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ብቻ ታጥሮ የነበረውን የሚዲያ ምህዳር በፋና ወጊነት ለመስበር ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡

ሆኖም ግን በምንሰራቸው ስራዎች በተለይም ፈር አልባ በሆነው የማህበራዊ ሚዲያዎች በአዘጋጆችም ሆነ በድርጂቱ ያልታሰቡ ጉዳዮችን ቃላትን በመሰንጠቅ ወደ አልተገቡ አስተሳሰቦች ለመውሰድ የተለያዩ አካላት ሲንቀሳቀሱ ተመልክተናል፡፡

ለአብነትም በቅርቡ በተላለፈው ኤልቲቪ ሾው በተባለው ፕሮግራማችን በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ የፖለቲካ ቡድኖችና መሪዎች ለዚች ሀገር የዲሞክራሲ ምህዳር መጎልበት የሚጫዎቱትን ሚና ለህዝብ ጥርት አደርጎ ለማሳየት የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን እየሰራን ስናቀርብ ብንቆይም በፕሮግራሙ ላይ የታዩ ጥቃቅን ችግሮችን ወደ ፈለጉት አቅጣጫ ለመጠምዘዝና በህዝብ መካከል ቅራኔን ለመፍጠር ያለመ ለማስመሰል ብዙ አካላት መንቀሳቀሳቸውን መነሻ በማድረግ የሚዲያ ተቋማትን የሚቆጣጠረው ተጠሪ መስሪያ ቤት ማለትም የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው ሀላፊዎችን ጠርቶ አነጋግሯል፡፡

ባለስልጣኑ ይስተካከሉ ባላቸው ጉዳዮች ማለትም የቃላት አጠቃቀም፤ወደ ብሄር ብሄረሰቦች ያዘነበሉ የሚመስሉ ጥያቄዎችና አስተሳሰቦች አንዲሁም መሰል ችግሮችን እድናስተካክል ምክር አዘል ማሳሰቢያ በመስጠትና አሁን በዩቱብ ገጻችን ላይ የሚገኘውን ፕሮግራም ከገጻችን ላይ እንድናነሳው ማሳሰቢያ ሰጥቶናል፡፡እናም ትዕዛዙን በመቀበል በትላንትና ዕለት ማንሳታችን ይታወቃል፡፤

ነገር ግን ይህንን ተከትሎ በበርካታ ተመልካቾቻችን ላይ ጥያቄ የሚፈጥሩ መልዕክቶች በፌስ ቡክ እየተራገቡ ይገኛሉ፡፤

ከሚነሱ ውዥንብሮች መካከልም ጣቢያው ሊዘጋ ነው፤ጋዜጠኛዋ ተባራለችና መሰል አሉባልታወች እየተገለጹ ይገኛሉ፡፡ሆኖም ግን አንዳቸውም ትክክል ያልሆኑና መሰረተ ቢስ ወሬዎች መሆናውን እየገለጽን አንድን ፕሮግራም ለመስራት ከአዘጋጁ በተጨማሪ በፕሮግራም ክፍሉና በይዘት ገምጋሚው ታይቶና ተፈትሾ የሚተላለፍ በመሆኑ የአንድ ግለሰብ ችግር ተደርጎ መቆጠሩ ትክክል ስላልሆና ጣቢያውም ችግሮች ካሉበት እየታረመ የሚስተካከል እንጂ ገና የረዥም ዓመታት ራዕይና ትልቅ ሀሳብ ያለው፤ከማንናው ብሄራዊም ሆነ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ወገንተኝነት የሌለው ድርጂት በመሆኑ ከውድ ተመልካቾቻችን ጋር አሁን የምሰራቸውን ብቻ ሳይሆን በቅርብ ይዘናቸው በምንቀርባቸው አዳዲስና ሳቢ ፕሮግራሞቻችን የበለጠ ተመልካቾቻችንን ለማስደስት የምንሰራ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ከገጻችን እንድናነሳው የታዘዝነውን ተንቀሳቃሽ ምስልም ወደ ነበረበት የመለስንና በቀጣይ በምንሰራቸው ፕሮግራሞችም የተሰጠንን ማስተካከያ ከግምት በማስገባት የበለጠ ያማሩና ጠንካራ የህዝብን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በመስራት እንደምንክሳችሁ እየገለጽን በስሜታዊነት ሳይሆን በጥልቀት እየተመለከቱ አስተያየት የሰጡንን አካላት በዚህ አጋጣሚ ለማመስገን እንወዳለን፡፡

ኤልቲቪ ለላቀ ህይወት

ከሰላምታ ጋር

ኤልቲቪ ኢትዮጵያ

Latest News

video image video image video image Read More

Get Connected

logo link youtube logo link twitter logo link facebook

Contact Information