Ethiopia: ጊዜው እንደት ይነጉዳል! በ2001 ወሎ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ነበርኩ ።

Woman in conference
ሙፈሪሀት ካሚል የአቡበክር አህመድ ህልም ነበረች !
የ እስላም ሀገሩ መካ
የወፍ ሀገሯ ዋርካ
ጊዜው እንደት ይነጉዳል! በ2001 ወሎ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ነበርኩ ።
ታዳ አሳይመንት ተሰጥቶን ፕረዘንቴሽን በምናቀርብበት አንድ ቀን ፋኢዛ እና ፎዚያ በሚባሉ መንትያ ጓደኞቼ ኒቃብ መልበስ ምክንያት ከስፖክን አስተማሪያችን ጋር ግጭት ተፈጠረ።
ሰበብ ፈልጎ የልቡን ጥላቻ አወጣው እንጂ ከገባበት እለት ጀምሮ የነሱ አለባበስ ምቾት እንደ ነሳው ፊቱ ያሳብቅ ነበር «ተገለጡና አቅርቡ፤አለዛ ውጡ»አለ።
ወጡ አጋጣሚ ሙስሊሞቹ 4 ብቻ ነበርን እኔም ለነሱ ከለላ ለመስጠት ያህል ክፍሉን ለቅቄ ተከተልኳቸው።
አስተማሪያችንም በድርቅናው እነሱም በአቋማቸው ፀኑ። ከትምህርት አገዳቸው።ነገሩ ተካረረና የግቢው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዘነበ መፍታት ከማይችለው በላይ ሆነ።
ይባስ ብሎ ሁሉም ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ እና ጅልባብ እንዳይለብሱ ምንም አይነት የእምነት መገለጫ በግቢ ውስጥ እንዳይታይ ውሳኔ ተላለፈ፤ ፋጡማ የምትባል የቢዝስ ተማሪ በዚሁ ምክንያት አቋርጣ ወጣች ።
የተወሰኑ ወንድም እና እህቶችም ታፍነው የገቡበት ጠፉ፣ ገሚሶቹ በቅጣት ተባረሩ። ነገሩን ለበላይ አካል አቤት ለማለት ከኛ በኩል ተማሪ ወክለን ወደ ባህር ዳር እና አድስ አበባ ብንልክም መልሱ እስኪመጣ ጫናውን መቋቋም ከበደን።
በዚህ ገፊ ምክንያት የደሴ እና የኮምቦልቻ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች በነቂስ የትምህርት ማቆም አድማ መተን ወጣንና ለሳምንት ያህል ሸዋ በር መስጅድ ሰፈርን።
በየ እለቱ የሸርፍ ተራ ሀብታሞች ይንከባከቡን ነበረ።
ስራችን ሙሀደራ ማዳመጥና በሆነው ነገር መብሰልሰል ብቻ ሆነ።
የዛኔ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ አድስ አበባ አልገባም ኑሮው ደሴ ነበረ ። ታዳ ሁልጊዜ በኒቃብ ምክንያት በሚደረግ አተካራ እሱ ይቆጣል! ይበሳጫል! ኒቃባችንን ከምናወልቅ ትምህርት እናቋርጣለን በሚሉ ልጆች አብዝቶ ይናደዳል።
«አንቺ ኒቃቤን አላወልቅም ብለሽ ከትምህርት ስትርቂ ታናሽ እህትሽ ሂጃቧን ትገፈፋለች፤ፀጉርሽን ሸፍነሽ ተማሪ እና የከልካዮችን ቦታ ያዥ ያኔ እህቶችሽ ሂጃብን በነፃነት ይለብሳሉ»ነበር የሚለው።
በወቅቱ ኡስታዝ ኒቃብን እንድህ እንደት ያግራራዋል እያሉ ቅር የሚሰኙ እህቶችም ነበሩ ። የሆነ ሁኖ ከሳምንት ወዳ ወደ ግቢ ተመለስን እኩሉ ተገልጦ፣እምቢም ያለ አቋርጦ አንጀታችን እንዳረረ ተመረቅን።
ሙፈሪሀትን ካየሁባት ቅፅበት ጀምሮ መላልሼም ሳያት ትዝ የሚለኝ አቡበክር አህመድ ነው።
የዛኔ ኡስታዝ አሻግሮ ያየው እኛ መመልከት ያልቻልነውን ሩቅ እውነት ነበር እሱ ያተገለጠለት ይሄ ቀን ነበር።
ሙፈሪሀት በለበሰቻት እራፊ ጨርቅ ምን ያህል ዎጋ ከፍላ ስልጣን ማማላይ እንደ ወጣች አላህ ይወቅ። እነሆ ዛሬ የአቡበክር ህልም እውን ሆኖ ሂጃባችን ቤተ_መንግስት ገብቷል። ከዚህ በህዋላ የሙስሊምን ልጅ ሂጃብ ለመግፈፍ የሚዳዳው ልበ ስንኩል በቁሙ ሙቷል።
በየሳምንቱ አርብ አይናችን እያየ ይቃጠል የነበረው ሂጃባችን ለቆሻሻ ታሪካቸው መደረቻ ቢሆን እንጂ አይደገምም!
«ኢትዮጲያ የክርስቲያን ደሴት ናት» የሚለው የከሀዲዎች ትርክት ውሀ በልቶታል።
የእስላም ሀገሩ መካ
የወፍ ሀገሩ ዎርካ!
ይሉት አፈታሪክ የቁም ቅዠት ሆኖ ቀርቷል።
“ዘመዶቻችን ሙሀመድ” የነበረ ስማቸውን “ወደ ማርቆስ” ለውጠው የእውቀት ጥማቸውን ያረኩበት ጨለማ የእብሪት ዘመን አክትሟል! እስላም እንደ ክርስቲያን ወገኖቹ ሁሉ አጥንቱን ከደሙ ገብሮ በሰራት ሀገር ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከከፍተኛ ትምህርትና ከፖለቲካው አለም እንድርቅ ይሰራበት የነበረው ለዘመናት የዘለቀ ሼፍጥ ፉርሽ ሆኗል።
ምንም እንኳ ዛሬ እየሆነ ያለው ነገር ቀድሞም እንደሚገባን ብናውቅም ተቀምተን ስለኖርን፣ የራሳችንን ነገር በሀይል ስለተነጠቅን የምናይ የምንሰማው ሁሉ ብልጭ ብሎ ድርግም የሚል ህልም ይመስለናል።
ከኛ በላይ የችግርን ገፈት የቀመሰ የለምና ለተጀመረው ለውጥ እና ለለውጡ አቀጣጣዮች ከማንም በላይ እንሰስታለን።
የፖለቲካ መስተጋብሩ የበለጠ እንዳብብ እና አቅም ያለውን ሁሉ ያማከለ እንድሆን ማንም የማይሳቀቅባት ኢትዮጲያ እንድትፈጠር እንትጋ!!
ተምር ሀሰን

Latest News

video image video image video image Read More

Get Connected

logo link youtube logo link twitter logo link facebook

Contact Information