Ethiopia: By Samuel Eyoub The shameful airline has now sunk into the process of unleashing and unfaithfulness.

እፍረተቢሱ አየር መንገድ ዛሬም አይኑን በጨው አጥቦ በክሕደት ላይ ተሰማርቷል።
ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ እንደጻፍነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዘረኝነትና የሙስና ካምፕ መሆኑ ይታወቃል። ይህ እውነት እስከዛሬ በደል በደረሰባቸው ሰዎች እየተመሰከረ ይገኛል።

ዘረፋንና ዘረኝነትን አጣምሮ የያዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ስር ነቀል የመዋቅር ለውጥ ሊደረግ ይገባል።የኢትዮጵያ አየር መንገድን በጥንካሬው ላይ ጥንካሬን ያቀዳጁት ውዱ ኢትዮጵያዊ አቶ ግርማ ዋቄ ተነስተው የዘረፋና የዘረኝነት ማኔጅመንት ከተመደበ ጀምሮ አየር መንገድ ላይ ከፍተኛ ሮሮ እና አቤቱታ እየሰማን እያየን ነው።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ጀምሮ እስከ መንገደኞች ድረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከፍተኛ የሆነ ስሞታ ያቀርባሉ፤ በተለያየ መንገድ በድርጅቱ ላይ የገጽታ ግንባታ ፕሮፓጋንዳ ቢሰራም አየር መንገዱን ከዘረፋና ከዘረኝነት ሊታደግ ባለመቻሉ ዘረፋውና ዘረኝነቱ አይኑን አፍጥጦ እያየነው ነው።

በተለያዩ የመስሪያ ቤቱ ቁልፍ መዋቅሮች ላይ የተመደቢ ዘራፊዎችና ዘረኞች አየር መንገዱን ለእዳና የዜጎችን መብት እንዲጣስ ከማድረጉም በላይ በከፍተኛ ደረጃ ሕገወጥ ስራዎች ይፈጸማሉ። የተለያዩ የሃገርን ኢኮኖሚ የሚጎዱ ኮንትሮባንዶች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ትእዛዝ ይሰራል ; ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡና ከሃገር የሚወጡ በርካታ ማቴሪያሎች የውጪ ምንዛሬዎች የተፈጥሮ ሃብቶች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በሕገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ የሃገሪቷን ኢኮኖሚ ባዶ አስቀርተውታል።
ዘረፋ ብቻ ሳይሆን አየር መንገዱ ዜጎችን ለማፈንና ሕጋዊ ተጓዦችን ለማስተጓጎል በሚደረገው ደሕንነታዊ ስራ ላይ ተባባሪ ነው፤ ዜጎች በነጻ እንዳይዘዋወሩ በሃገር ውስጥና በውጪ በረራዎች ላይ ሰላዮችን በመመደብ ወንጀል ላይ የ አየር መንገዱ ማኔጅመት ተሳታፊ ነው። በርካታ የደሕንነቱን መስሪያ ቤት ወንጀሎችን በማስፈጸም ረገድ ሚናው የላቀ ነው።ከአየር መንገዱ በርካታ ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ እምነታቸውና በዘራቸው እየተመረጡ ተባረዋል። እንዲሁም ያገኙትን እድል በመጠቀም ከሃገር የሸሹም በርካቶች ናቸው። ይህ አየር መንገድ ከደሕንነት ተቋሙ የተቀበለውን ትእዛዝ ወደ ተግባር በመለወጥ ዘረኝነት በድርጅቱ ውስጥ እንዲነግስና የተወሰኑ የገዢው ሰዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲሰራ ቆይቷል።
ሳይቀረጥባቸው በርካታ እቃዎች በመንግስት ባለስልጣናትና ዘመዶቻቸው በሕገወጥ መንገድ በገፍ ገብተው የግብር ከፋዩን ነጋዴ እንቅስቃሴ ከጨዋታ ውጪ እያደረጉ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በአሁን ወቅት ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት ሲዘርፉ የኖሩ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች ከነዘመዶቻችው የአየር መንገዱን ሰራተኞች በመጠቀም የውጪ ምንዛሬ እያሸሹ ይገኛሉ። ይህ ከፍተኛ ቁጥጥር ካልተደረገበት አደጋው የከፋ ነው። ወደ ዱባይ የሚሸሹ የውጪ ምንዛሬዎች ማረፊያቸው ማሌዢያና ፓናማ ባንኮች ነው። አየር መንገዱ ሊፈተሽ ፣ ሊጠራና ሊበረበር እንዲሁም ስር ነቀል ለውጥ ሊደረግበት ይገባል።

The shameful airline has now sunk into the process of unleashing and unfaithfulness.
The Ethiopian airline, as we have noted so far, has been known as a racist and corrupt camp. This truth is being witnessed to people who have been persecuted for the past time.
The Ethiopian Airlines, which combines robotics and racism, needs to be transformed into a fully-fledged Ethiopian airline. We have seen the Ethiopian Airline, Girma Wuki, who has been a strong driver of assault and racial retribution, and we are hearing a lot of airplanes and complaints.
From Ethiopian trainers to passengers, there is a great deal of dysfunction in the Ethiopian Airlines, despite the fact that he has made a theme of propaganda on the organization, he is glazing over the glare of the airline.

Assemblies and racists at various locksmith-like institutions have made the airline unlawful for the rights of citizens and the rights of its citizens, and the high level of illegal activities. Regulations affecting various economic sectors of the country are subject to a higher governmental order; Many domestic and foreign-invested natural resources, foreign exchange reserves, empties of Ethiopian air charter, emptied the economy of the country.

It is not only a robbery, but of course, the airline is an integral part of the airline pilots to expedite citizens and to legitimize legitimate business travelers. Many of the Ethiopians have been mired in their political beliefs and race. They are also many of the FDI-backed countries using the opportunity they have. By changing the order from the safety institute, the airline has been working to ensure that racism can be regrouped in the company and some of the buyers benefit.

Many unprotected government officials and their relatives are illegally entering and outlining the taxpayers’ business. Not only that, but officials and investors who have now sprung out in the past twenty-seven years have been using their expedition to expedite foreign currency. If this is unmanaged, the risk is greater. Maldives and Panama banks are home to Dubai’s foreign exchange reserves. The airline needs to be tested, called and shifted, and radical changes need to be made.

Latest News

video image video image video image Read More

Get Connected

logo link youtube logo link twitter logo link facebook

Contact Information