የዲያስፖራው ሠራዊተ ውዥንብር

ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያከናነበውን የበደልና ኢሰብዓዊ ሥርዓት እድሜ ለማራዘም ዛሬን

ተንተርሶ እስከ ወዲያኛው ወገኖቻችንን አራርቀውና አጠላልፈው ሊያቆዩ የሚችሉ እኩይ

ዘዴዎችን ተጠቅሟል። እየተጠቀመም ነው። ወያኔ ከተለያየ አቅጣጫ የሕዝብ ግፊት

ስለበረታበትና በሕዝባዊ እንቢተኝነት ስለተርበተበተ ማዳከሚያና መበታተኛ አድርጎ

የሚጠቀመው፣ ማስፈራራትና ሃይል መጠቀምን ቀላቅሎ፣ የተለሳላስና ሰላም ፈላጊ በመምሰል

ታዋቂ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በጥቅም ሸንግሎ መያዝ በአሁኑ ሰዓት ጎልተው ከሚታዩ

ዘዴዎቹ ውስጥ ናቸው። ግን ከተጠቀመባቸው በኋላ አላምጦ የሚተፋቸው ትቂቶች

አይደሉም።

ለኢትዮጵያ ሙስሊም ሕዝብ ድምፅ ይሆናሉ ተብለው በተለይም በዲያስፖራ የተቋቋሙ

ድርጅቶችና እውቀት አላቸው የተባሉ ግለሰቦች ሣይቀሩ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ “ብሔራዊ

ጭቆናን” ከጫንቃዬ ለማውረድ እየታገልኩ ነው እያለና ከፍተኛ መስዋዕት እየከፈለ ባለበት

ወቅት፣ እነሱ ግን ወያኔ “ልማታዊ መንግሥት” ነኝ የሚለውን በሚያንፀባርቅና በሚያስተጋባ

መልኩ የዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ሕብረተሰብ እየሰበሰቡ ውዥንብር እየነዙበት

ይገኛሉ።

በጅማ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ ለመክፈት የተሰበሰበው ሙስሊም በሕወሃታዊው መጅሊስ

እንዲሁም በደህንነትና ካድሬዎች ትዕዛዝ ሰሞኑን በወታደር ተበትኗል። የወልዲያ ሙስሊሞች

ለረመዳን ፆም ዝግጅት የመስጊዳቸውን ምንጣፍ በአዲስ እንዳይተኩ ታግዳዋል። ጉድ በሉ!

አሮጌውንም እንዳያጥቡ ተከልክለዋል! የመስጊዱን ውስጥ ለመጥረግ ፈቃድ ያስፈልግ ይሆን?

ለወገን ነፃነትና ለፍትሕ በመሟገታቸው የዚህ ትውልድ ምርጥ የአገሪቱ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣

የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ መለዮ ለባሾች፣ የሃይማኖት መሪዎች፡- እነ አህመዲን ጀበል፣ እነ

ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና፣ እነበቀለ ገርባ፣ እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ እነኮለኔል

ደመቀ ዘውዱ እና እነ ሸህ አዳኖ የመሰሰሉ የቁርጥ ቀን ልጆች በወያኔ እሥር ቤት እየማቀቁና

እየተሰቃዩ እነዚህ በዲያስፖራ የመሸጉ የውዥንብር ሰራዊቶች በሃገራችን ፍትህ እየመጣ ነው

እያሉ ሲወሸክቱ እንሰማቸዋለን።

ብዙዎች የእለት ጉርስ አጥተው ከሕፃን እስከ ሽማግሌ በረሃብ እየረገፉ፣ በጣት የሚቆጠሩ

ባለጊዜዎች በጠራራ ፀሓይ ነጋ ጠባ ሚልዮን ዶላር በሻንጣ እያጨቁ በስርቆት ወደውጭ አገር

ሲያግዙ “እየለማን ነው” ይባላላል። ኢኮኖሚያችን ከሰማይ ብልጭታ በላቀ ፍጥነት እያደገ ነው

ይባላል። የውዥንብር ሠራዊቶቹም በያሉበት ይህንን እንደገደል ማሚቶ ሲያስተጋቡ

የሚያሳዝነው በኩራት ተወጥረው መሆኑ ነው።

የኦሮሞና የአማራ፣ የአኙዋክና የኮንሶ ወጣቶች ከያሉበት እየታደኑ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ

በአዋሽ፣ በአላጌና በብር ሸሎቆ ጦር ካምፖች ታጉረው በእርማትና ስልጠና ስም ለበሽታና

ለራሃብ ተዳርገው እንደቅጠል እየረገፉ ባሉባት አገር ለመሆኑ እነማን ናቸው እያደጉ ያሉት?

ያገሪቱ ልማት ማንን ነው ያለማው? መልሱን ሁላችንም ስለምናውቀው እጅ ማውጣት

አያስፈልግም።

የወያኔ መንግሥት ለስልሷል፣ ዳእዋ ያለገደብ በአገሪቱ እየተናኘ ነው፣ መስጊድ ሥራ ላይ

እንበርታ! በርቱ! ብለው ጥሪ ያቀርባሉ። አባቶቻችን በአንጡራ ሃብታቸው ያሠሩዋቸው

መስጊዶቻችን በደህንነቶች ትዕዛዝ ተነጥቀው ለአህባሾችና ለካድሬ ኢማሞች እንዳልተሰጡ

ሁሉ። በኢስልምና ዕውቀታቸውና በእድሜ ባለፀጋነታቸው አንቱ የሚባሉ ኢማሞቻችን

ባሰገዱባቸው መስጊዶቻቸው ውስጥ አይዋረዱ ውርደት ተዋርደዋል። በሃሰት ክስ

ተመሥርቶባቸው ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ ታስረዋል፣ ብዙዎች ካገርም ተባረዋል። ወጣት

ሙስሊሞች በሰንካላ ምክንያቶች ከትምህርትና ከሥራ ገበታ በየእላቱ በወያኔ ካድሬዎች ትዕዛዝ

እየተመነጠሩ ነው። ብዙዎች በሃሰት ክስ ፍርድ ቤት እየተመላለሱ ነው። በረሃብ በተመቱ

አካባቢዎች እንኳን ሳይቀር ነፍስ አድን ከውጭ የመጣ እርዳታ ሲታደል ማን መሞትና ማን

መኖር እንዳለበት የሚወሰነው በፖለቲካ አቋምና ዘርን መስፈርት በማድረግ ነው። ይህ ዓይነት

መሰል ወንጀሎች በወያኔ ሥርዓት እየተፈፀሙ ባለበት ሰዓት እነሆ መስጊድ አሰሩ እየተባለ

በወያኔ የውዥንብር ሠራዊቶች አማካይነት በዲያስፖራ ቅስቀሳ በስፋት እየተካሄደ ነው።

ለሙስሊሞች መስጊድ የስግደት፣ የማስተማሪያና የመማሪያ፣ በደስታም ሆነ በመከራ ጊዜ

የመገናኛ ማዕከላችን ነው። ዳእዋ ወደአላህ የምንጣራበት፣ ወደቀናው መንገድ አመላካችና

የዕምነታችን ማጥበቂያ ገመድ ነው። እኛ እየታገልን ዳእዋ እናድርግ፣ ዳእዋ እያደረግን እንታገል

ባዮች ነን። በመሬት ላይ ያለው ክስተት አዲስ መስጊድ መስራትና ዳእዋ ብቻ የማድረጊያ

ሳይሆን መስጊዶቻችንን በመንጠቅ ዳኢዎቻችንን የሚገድለውን፣ የሚያሰድደውን፣

የሚያዋርደውንና የሚያሥረውን የወያኔ ሥርዓት ከጫንቃችን ላይ አሽቀንጥረን መጣልም

ጭምር መሆን ይገባዋል ነው የምንለው።

አንዳንድ በተለይም በዲያስፖራ የኢትዮጵያውያን የሙስሊም ድርጅቶች የወያኔ ፕሮፓጋንዳ

ሰለባ በመሆን ጭልጥ ብለው በወያኔ ጀልባ ተሳፍረው የሙስሊሙን ትግል ለመጉዳትና

ለማዳከም የተቻላቸውን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ትግሉ አፍላ በነበረበት ወቅት ነበር። ይህ

ሁሉ በደል በሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ወያኔን ተለማመጡ፣ በአገሪቱ ሰላም ሰፍኗል፣ የልማት ቅላፄ

አዚሙ እያሉ ቅስቀሳውን ዛሬ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ አጣጡፈውታል። ከዚህ ጋር በተያያዘ

ከአሚሮቻችን ጋር በቂልንጦ እስር ቤት አሰቃቂ ግፍ የተፈፀመበት ጀግናው ሃብታሙ አያሌው

በአሚሮቻችን ላይ የደረሰውን አስደንጋጭ ክስተት አስመልክቶ በቅርቡ በሰጠው ቃለ ምልልስ

የምስክርነት ቃሉን ሲሰጥ “ከዲያስፖራ የመጣው የሙስሊሞች ድርጅት” ማለትም “በድር”

መሆኑ ነው “ኡስታዞቹ በጉልበታቸው ተንበርክከው፣ ጥፋተኛ ነን ብለው ወያኔን ይቅርታ

ጠይቀው ከእሥር እንዲፈቱ” ወጥሮ ይዟቸው ነበር ብሏል። እነኡስታዝ ሃሰን ታጁን

ሕዝበሙስሊሙ አንቅሮ የተፋቸው እርስ በርሳቸው ተመራርጠው የሄዱት የበድር ሽማግሌዎች

እንዳስተጋቡት ሁሉ “ጥያቄዎቻችን ተመልሰዋል፣ የቀረው የታሰሩት አሚሮቻችን መፈታት ብቻ

ነው” የሚል ስሜት ያዘለ ሃሳብ በመሰንዘራቸው አልነበረምን?

የወያኔን እኩይነት የተረዱና ግልጽና የማያሻማ አቋም ይዘው ወያኔን በመፋለም ላይ ያሉ

ድርጅቶችና ግለሰቦች ከበድር የሽምግልና እንቅስቃሴ በስተጀርባ የወያኔ አቀንቃኞችና

ጥቅመኞች እንዳሉበት በመጠቆም በድር ይህን የዲያስፖራውና የአገርቤት ሙስሊሞች ከዳር

እስከዳር ያወገዙትን የመሃል ሰፋሪነትና ያሸማጋይነት ተግባር እንዲያቆም ወንድማዊ ምክር

በጊዜው ለግሰው ነበር። የተባለው ሽምግልና በሙስሊሙ መካከል ክፍፍልና ብዥታን

በመፍጠር ወያኔ የሚመኘውን የትግሉን መዳከም ከመርዳት ባሻገር ውጤት አልባና ትልቅ

ኪሳራ የሚያስከትል መሆኑን ተቆርቋሪዎቹ ጨምረው አስጠንቅቀው ነበር። ሌላው ቀርቶ የበድር

የሽምግልና ቡድን ቅሊንጦ ሄዶ ከአሚሮቻችን ጋር የተገናኘው በአምባሳደር ግርማ ብሩ

መሪነትና በቂልንጦ የደህንነትና ጥበቃ ባለሥልጣናት አጀብ ነበር። ለመሆኑ በገራፊና በአሳሪ፣

በተገራፊና በታሳሪ መካከል ምን ዓይነት ሚዛናዊ ውይይት ሊደረግ ይቻላል ተብሎ ተገምቶ

ነበር?

አሚሮቻችን በበኩላቸው የበድር ተወካዮችን “ለምን መጣችሁ?” ብለው ሲጠይቋቸው

“ጤንነታችሁን ለመጠየቅ ነው” የሚል መልስ እንደሰጧቸው ጠቁመው ሽምግልና የሚባል ነገር

እንዳልተከናወነ ከጊዜ በኋላ ገልፀዋል። በጣም የሚገርመው፣ ካፈርኩ አይመልሰኝ እንዲሉ፣

የበድር ሽማግሌዎች ወኪል በአንድ የሬድዮ ጣብያ ቀርቦ “በመንግሥትና በሕዝበሙስሊሙ

መካከል ድልድይ ዘርግተን፣ የበድር ቢሮ ለመክፈት በሚያስችል ሁኔታ አመቻችተን፣ ተልዕኳችን

ስኬታማ ሆኖ ነው ከአገርቤት የተመለስነው” ብሏል። ይህ ወኪል ሳይጠቅስ የዘለለው ዘረጋነው

ያለውን ድልድይ እንዲጠብቅ ውክልና የሰጡት ግለሰብ አህባሽ ዘመም መሆኑን ነው።

አሁንም ወያኔን ወያኔ ማለት የማይቻልበት፣ በኦሮሞ፣ ባአማራው፣ በአኙዋኩና በኮንሶ

ወገኖቻችን ላይ የሚፈፀመው ጭፍጨፋ የማይወገዝበት፣ የሕዝበ ሙስሊሙን አንድነት

ለማረጋጥ የሚጠቅሙ አርእስቶች ለውይይት የማይቀርቡበት ስብሰባ የምትዘጋጁ ወገኖች

በታሪክም ሆነ በአላህ ፊት ብዙ የምትመልሱት ጥያቄ እንደሚጠብቃችሁ አትጠራጠሩ። እኛም

ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ብዙ መሥዋዕትነት የከፈሉበትን የሕዝበሙስሊሙን ሰላማዊ

ትግል የመጠበቅ ሃላፊነት ስላለብን ዕውነት መናገራችንን አናቆምም።

አንድነት ከጥራት ጋር!

አላሁ አክበር!

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት

Latest News

video image video image video image Read More

Get Connected

logo link youtube logo link twitter logo link facebook

Contact Information